በኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት ወቅት 2009 ዓ.ም በኦሮሞ ታጋዮች ፋውንዴሽን እና ቱምሳ ዴቬሎፕመንት ግሩፕ የተቋቋመው እርቡ ጀኔራል ቢዝነስ ግሩፕ ኃ.የተ.ዩግ.ማህበር በ10,000,000.00 የተከፈለ ካፒታል የተነሳ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ30,090,000.00 የተከፈለ ካፒታል፣ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ቋሚ ንብረት ያፈራ ሲሆን እስከ አሁን ከ4,000 በላይ የጥበቃ እና የፅዳት ሠራተኞች ለተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ ተቋማት አቅርቦ እያሰራ ሲሆን በዋና መ/ቤት እና በአገሪቱ በከፈታቸው ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ከ70 በላይ አመራሮች እና የስታፍ ሠራተኞችን በመቅጠር አሰማርቶ በጥብቅ የሥራ አመራር እና የቁጥጥር ስልት በማገልገል ላይ የሚገኝ ግዙፍ ድርጅት ነው፡፡በተሰማራባቸው የጥበቃ እና የጽዳት አገልግሎት በፊንፊኔ ከተማ፣ በየክልሎች /በተለይም በኦሮሚያ ክልል በብዙ ከተማዎች/፣ በድሬደዋ ከተማ አስተዳደር እና በሌሎች ቅርንጫፍ መ/ቤቶች በመክፈት ከዋና መ/ቤት እስከ ቅርንጫፍ መ/ቤቶች የአመራር የተቀላጠፈ ስራ እየሰራን እንገኛለን፡፡
In 2025 IRBU is a leading company in providing a cleaning and security service and high-quality product supplier in East Africa.
© 2022 Created By African Sunrise